እራስን መሆን ምን ማለት ነው? ማንነታችንን ለመግለፅስ እንዴት እንችላለን ?ለዘመናት ከተቃራኒ ፆታ አፍቃሪነት ውጪ ያሉ የማህበረሰብ ክፍል ተደብቀው እና ስለማንነታቸው የሚገልፁበት ቃላትን አተው ኖረዋል። የሺህ ዘመናት የጥላቻ ንግግሮች ሰርፀው ገብተው ማን ነኝ ለሚለው ጥያቄ ለመመለስ እንኳ ቃል አሳጥቶ መና አስቀርቶናል። ለዚህ ነበር የዜጋው(LGBTQI2S+) ማህበረሰብ በየጊዜው አዳዲስ ቃላትን መጠቀም መፍጠር ግን ያለው። አሁንም እንደ ሰው ሙሉ ውበታችንን የማንነታችንን አንዱን ፆታዊ ክፍል የሚገልፅ ቃላት መፈለግ አላቆምንም የተሻለ ክብር እና አቅም የሚሰጥ ቃል መፈለግ ጥላቻን የመቃወም አንድ እርምጃችን ነው!
በዛሬው ፅሁፍ ይህ በተደጋጋሚ ራሳችንን ለመግለጫነት የምንጠቀመው ቃል ታሪካዊ አመጣጡን እንዲሁም በውስጡ አቅፎ ስለያዛቸው አካላት በሙሉ በትንታኔ ለማየት እንሞክራለን።
በመጀመርያ LGBT የሚለው ቃል ይህንን የሚደግፉ አክቲቪስቶች እ.ኤ.አ በ1980ዎቹ እና 1990ዎቹ ውስጥ Lesbian፣Gay፣Bisexual እና Transgender ን ለማካተት መጠቀም ሲጀምሩ ብቅ ያለ ምህፃረ-ቃል ነው።ይህ ምሕፃረ-ቃል በ 1990 "Q"(Queer)ን በማካተት በጥቅም ላይ ውሏል።
አሁን ደግሞ LGBTIA2S+ የሚሉትን ከዚህ በታች በዝርዝርን እንመለከታለን
L (lesbian)
ከሴቶች ጋር ብቻ የጾታ ወይም የፍቅር ስሜት የሚሰማቸው፤ደስታና እርካታቸው ከሴቶች ጋር የተገደበ ሴት እህቶቻችን ናቸው። አንድ ሴት ሌዝቢያን መሆኗን በመመልከት ብቻ ለማወቅ የሚያስችልት መንገድ የለም።
Lesbian በ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ታዋቂ ገጣሚ ከነበረችው Sappho መኖሪያ ከሆነችው የግሪክ ደሴት Lesbos የተወሰደ ስያሜ እንደሆነ ይነገራል።
ከ Sappho ግጥሞች ውስጥ የተወሰኑት ነገራቶችን ተቋቁመው እንዳሉ ይነገራል እነዚህ ግጥሞቿ ላይ በዓበይት ርዕስነት የሴቶችን የዕለተ ዕለት ኑሮ፣ግንኙነታቸውን፣የአምልኮ ሥርዓቶቻቸውን፣በሴቶች ውበት ላይ ትኩረት አድርጋ የፃፈቻቸው ግጥሞች እንዲሁም የፍትወት ስሜትን ያወጣችባቸው ግጥሞች ይጠቀሱበታል። ለሌሎች ሴቶች ፍቅርን ለመግለፅ በምትፅፋቸው ግጥሞች ውስጥ "lesbian" የሚለውን ቃል ለሌሎች ሴቶች የሚስቡ ሴቶችን በማመልከት አስተዋፅኦ አድርጎላት ነበር Sappho ለሴት ልጅ ያላት ፍቅር በገሃድ ያሳየችባቸው እንደሆኑም ይነገራሉ።
በየአመቱ April መጨረሻ ሳምንት Lesbian Visibility week በመባል በዓለማቀፋዊ ሁኔታ ተከብሮ ይውላል እነሱንም የሚገልፀውን መለያ ሰንደቃቸዋ ቀጥሎ ያለው ነው።
G (gay)
ለሌላ ወንድ በፆታ እና በፍቅር የሚሳቡ ወንዶችን ያመላክታል እነዚህም የ ተመሳሳይ ፆታ አፍቃርያን(Homosexual) አካላቶች Gay በመባል ይታወቃሉ።ይህ ቃል ለጠቅላላ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ቡድኖችን ለመግለፅ ልንጠቀምበት እንችላለን ይሁን እንጂ በዋነኝነት ወንድ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃርያንን አጠቃለን እንጠራበታለን።
Gay የሚለው ቃል ታሪካዊ አውድ “cheerful” ወይም “carefree” ማለት ነው። ቃሉም በ 20 ኛው ዘመን አጋማሽ ላይ ታዋቂነትን አግኝቷል።
ስለ Gay ስናሰሳ Karl Heinrich Ulrichs ቀደም የምናገኘው ስም ነው በዘመናችን ለመጀመርያ ግዜ በአደባባይ የወጣ ወንድ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ "Gay" አክቲቪስት እንደሆነ በብዙዎች ዘንድ ይታወቃል።
እ.ኤ.አ August 1825 በ ሰሜን-ምዕራብ ጀርመን የተወለደው Ulrichs ገና በልጅነቱ የሴቶችን ልብስ በመልበስ ከሴቶች ጋር ጓደኝነት መመሥረትን ይመርጣል ሴት ልጅ የመሆን ፍላጎቱንም ጎን ለጎን እያያያዘ ይገልፃል።
Ulrichs የሕግ እና ሥነ-መለኮት ትምህርቱን በ Göttingen University 1946 ላይ ተመርቋል።በዚሁ አመት በበርሊን ዩኒቨርሲቲ ታሪክ አጥንቶ በላቲን ቋንቋ የዌስትፋሊያ የሰላም ስምምነት ፅፏል። ከዚያም በሃኖቨር ሲቪል ሰርቪስ ውስጥ እስከ 1854 ድረስ ሠርቷል እሱም በተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪነቱ ከሥራው ከመባረሩ በፊት ሥልጣኑን በገዛ ፍቃዱ ለቀቀ። ምንም እንኳን በሃኖቨር ውስጥ የተመመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ሕገ-ወጥ ባይሆኑም ከሲቪል ሰርቪስነቱ ሊባረረው ግን ይችል ነበር ይህ ሰው ለሌሌች LGBTQ+ ደጋፊ አክቲቪስቶች እንደ መነሻ ጥንካሬ ሰጥቷቸዋል።
በየዓመቱ June 28 የወንድ ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ Gay የኩራት ቀን ተደርጎ በአለማቀፋዊ ሁኔታ ተከብሮ ይውላል።እነሱንም የሚገልፀውን መለያቸው ቀጥሎ ያለው ነው። እነሱንም የሚገልፁ መለያዎችም ቀጥሎ ያሉትን ይመስላሉ።
B(Bisexual)
“ሁለት ሴክሹዋል” የሚለው ቃል በአንድ ፆታ ላይ ብቻ ያልተገደበ የፍቅር እና/ወይም የወሲብ ስሜቶች የሚያስተናግድ(የሚፈፅም) ሰውን ለመግለፅ ያገለግላል። ከራሱ ጋራ ተመሳሳይ ፆታ ወይም ለተቃራኒ ፆታ ወሲባዊ ተማርኮ ያለውን ወንድ ወይም ሴት የሚገልፅ ቃል ነው።
ጥናቶች (bisexual) ሰዎች በአጠቃላይ ከ gay፣Lesbian እና ከ straight ሰዎች ይልቅ ከአንድ በላይ ጋብቻ ለመፈፀም ክፍት እንደሆኑ፤እንዲሁም የረጅም ጊዜ አንድነት የተሞላበት ግንኙነት የመፍጠር እድላቸውም ሰፊ እንደሆነ ይገልፃሉ።ነገርን ግን bisexual ሁለቱንም ፆታዎች 50 50 በሆነ መልኩ ይመለከታል ወይም ለ ሁለቱንም እኩል የሆነ አመለካከት ላይናረው ይችላል።ለሁለትዮሽ የፆታ መሳብ ጵንሰ-ሃሳብ በባዮሎጂ፣በስነ-ልቦና እና በጾታዊ ግንኙነት ውስጥ መፈጠሩ በ 19 ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ በይፋ መታወቁ ይነገራል።
ሌሎች ጥናቶች እንደሚያመላክቱት bisexual የሆነ ሰዎች ከሚደርስባቸው አለው ባይ ማጣት እና ከሚደርስባቸው ጥላቻ (በዜጋው ኮሙኒቲሞ ጨምሮ ልክ ያልሆኑ አመለካከቶችን ጨምሮ) ከሌሎች ፆታዊ ተማርኮ ካላቸው አካላት ጋር ሲነፃፀርለ ለጭንቀት ፤መንፈሳዊ ጭንቀት፤እንዲሁም ለ ራስ ማጥፋት ይጋለጣሉ።
በአለም አቀፍ Jun 28 የ bisexual የኩራት ቀን ተብሎ ተከብሮ ይውላል።
እነዚህን አካላት ለመግለፅ እንደመለያነት የምንጠቀምባቸው አርማዎች ቀጣይ ይገኛሉ።
T(transgender)
የፆታ ማንነታቸውን፣የፆታ አገላለፃቸውን እንዲሁም ባህሪያቸውን በተለምዶ በተወለዱበት ግዜ ከተመደቡበት ፆታ ጋር የማይጣጣምላቸው ሰዎችን ለማመላከት የምንጠቀምበት ጃንጥላ ቃል ነው። ትራንስጀንደር ሰዎች የፆታ መለያቸው ሲወለዱ ከታሰበው ጾታ የተለየ ነው።trans ትራንስጀንደር የሚለውን ቃል በማሳጠር ልንጠቀምበት እንችላለን በተለምዶ ስንወለድ ያዋለደን አካል ሰውነታችንን በመመልከት ወንድ ወይም ሴት ሲል ይሰይመናል ነገር ግን ትራንስ ሰዎች ያን የፆታ ስያሜ አይቀበሉትም ወይም ያ ፍፁም ማንነታቸው እንዳልሆነ ያምናሉ ።
ሁሉንም ያካተተ ባይሆንም አንዳንድ ትራንስ ሰዎች ሊለዩባቸው የሚችሉ ውጫዊ ገፅታዎች አሉ ከነዚህም ውስጥ ሲወለዱ ወንድ ተብለው የሚጠሩ ሰዎች ፦ትላልቅ ተረከዝ ያላቸውን ጫማ መጫም፣የድምፅ አወጣጥ ቅላፄ፣የቆዳቸው ሁኔታ እንዲሁም የወገባቸው ኩርባነት ለመለያ የሚጠቅሙ ጥቂት ምልክቶች ናቸው።
እንዲሁም ሲወለዱ ሴት ተብለው የሚጠሩ ሰዎችም፦የቆዳቸው ሁኔታ፣የፀጉሮቻቸው አበቃቀል፣የጡንቻዎቻቸው ግዝፈት እንዲሁም የጡቶቻቸው መጠን እንደ አንድ ምልክት ሊገለፁ እንደሚችሉ ይታሰባል Trans ሰዎች የስርዓተ-ፆታ Dysphoria ሊያጋጥማቸው ይችላል።
Dysphoria አቻ ትርጉሞ የመረበሽ ሁኔታ ወይም አጠቃላይ የህይወት እርካታ ማጣት የሚለው ነው።Dysmorphic Disorder (BDD) አንድ ሰው ስለ አካላዊ ገፅታ ጭንቀት እንዲሰማው የሚያደርግ የ የስነልቦና እክል እንደሆነ ይታወቃል።ካለውና በውልደት ከሚጠራበት ፆታ ጋር ባለመጣጣም ምክንያት ለ ከፍተኛ ጭንቀት የሚያጋልጠው የስነ-ልቦና ችግር ተጠቂ ሊሆኑም ይችላል።
ከላይ ባለው ዝርዝር ሁኔታ የተነሳ አንዳንዶች የ transgender ቀዶ ጥገናን በማድረግ ከሚጣጣሙት የፆታ ማንነታቸው ጋር በተሻለ መልኩ በመገናኘት አካላዊ በባህሪያትን በመላበስ የተሻለ ደስተኛ ህይወትን እንዲገፉ ያስችላቸዋል።እነዚህ ቀዶ ጥገናዎች በሁለቱም ፆታ የተለያየ የመከፋፈል ሂደቶች አሏቸው እንዲሁም እንደየ ግለሰቡ ፍላጎቶች የተለያዩ ቴክኒኮች እና ግቦች ይኖራሉ።
March 31 በ (TDOV | Transgender Day of Visibility) ስለ transgender ግንዛቤን ለማሳደግ፣አንዳንዶች ላበረከቱት አስተዋፅኦ እውቅናን ለመስጠት እንዲሁም ልዩነታቸውን በማክበር የትራንስ ኩራት ቀን በዓለም አቀፍ በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ይውላል።እነዚህን አካላት የሚገልፁ መለያዎች የሚከተሉት ናቸው
ሁለተኛውን ክፍል ይዘን የምንቀርብ ይሆናል