◈አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster) ምንድን ነዉ ?
▸አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster) በቆዳ ላይ የሚወጣ ሕመም ያለው ሽፍታ ሲሆን (Varicella zoster) በሚባል ቫይረስ አማካኝነት ይከሠሰታል።
▸ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ 20% በመቶ የሚሆነው የዓአለማችን ሕህዝብ በዚህ በሽታ ይጠቃል፡፡
▸ይህ ሕህመም የሚከሠሰተው አስቀድሞ ጉድፍ (Chickenpox) በተያዙ ሰዎች ላይ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን ሰዎቹ በጉድፍ በሽታ ተይዘው እንደነበረ ላያውቁ ወይም ላያስታውሱ ይችላሉ።
◈የአልማዝ ባለጭራ በሽታ መንስኤዎች :-
▸ጉድፍን( Herpes Zoster) (Chickenpox or Shingles) የሚያስከትለው ቫይረስ ሲሆን በሽታው ከዚህ በፊት ጉድፍ የነበረባቸውን ሰዎች ያጠቃል፤ ሆኖም አደገኛ የሚባል አይደለም። ይህ በሽታ ምናልባት ሌሎች እንደ ካንሰር ወይም ኤድስ የመሳሰሉ አደገኛ በሽታዎች እንደ ማስጠንቀቂያ ሊታይ ይችላል
◈ Herpes zoster) እንዴት ይከሠሰታል?
▸ ቫሪሴላ - ዞስተር ሰዎች በጉድፍ እንዲታመሙ የሚያደርግ ቫይረስ ሲሆን፤ ህመሙ ወደ ሰዉነት ካለፈ በኋላ ይህ ቫይረስ በአከርካሪ እና በአንጎል አቅራቢያ በሚገኙ ነርቮች ውስጥ ይቀመጣል።
▸ አመቺ ሁኔታን ሲያገኝ ይህ ቫይረስ በነርቮች ውስጥ በመጓዝ በቆዳችን ላይ አልማዝ ባለጭራ በሽታ እንዲከሠሰት ያደርጋል።
◈ለአልማዝ ባለጭራ መከሠሰት አመቺ ሁኔታዎች?
▸ የሰዉነት በሽታ የመከላከል አቅም የሚቀንሱ ሁኔታዎች (ህመሞች)።
• ኤች አይ ቪ ኤድስ ህመም
• የካንሰር በሽታ ወይም የኬሞቴራፒ ሕክምና
• አንዳንድ መድኃኒቶች (Steroids)
• ከፍተኛ ውጥረት ወይም ጭንቀት
• ዕድሜ በተለይም ከ 50 ዓመት በላይ
◈የአልማዝ ባለጭራ ምልክቶች
• አልማዝ ባለጭራ ማንኛውንም የሰውነት ክፍል ሊያጠቃ ይችላል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ግን በአንድ ጎን በኩል በደረት፣ በሆድ ወይም በጀርባ ላይ ሊወጣ ይስተዋላል።
• ይህ ህመም ቆዳ ላይ ሽፍታ ከማሳየቱ ጥቂት ቀናት አስቀድሞ የመደንዘዝ፣ የማቃጠል እና የማሳከክ ስሜት ይኖረዋል።
• ይህ ስሜት ከታየ 1 ወይም- 2 ቀናት በኋላ በአንድ የሰውነት ጎን ብቻ የቆዳ መቆጣት እና ዉሃ የቋጠረ፣ ሕህመም ያለው ሽፍታ መታየት ይጀምራል።
• ብዙ ጊዜ ሽፍታው ከጥቂት ቀናት በኋላ መድረቅ እና መክሰም ይጀምራል፡፡ ከዚያም በአንድ1 ወይም ሁለት2 ሳምንት ውስጥ ይጠፋል።
• በተጨማሪ ትኩሳት ፣ ድካም፣ ራስ ምታት እና ህመሙ በተከሰተበት አካባቢ ንፍፊት (Lymphadenopathy) መውጣት ሊኖር ይችላል።
◈ አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster) ተላላፊ ነው?
▸ ታማሚዎች በቀጥታ አልማዝ ባለጭራን ማስተላለፍ አይችሉም ። ነገር ግን የጉድፍ ክትባት ያልወሰደ ወይም ጉድፍ ታሞ የማያውቅ ሰው በታማሚው አካባቢ በሚሆንበት ጊዜ በጉድፍ በሽታ ሊጠቃ ይችላል።
▸ ቫይረሱ ከታማሚው ሰው ጋር በሚደረግ ቀጥታ የቆዳ ንክኪ ወይም በትንፋሽ አማካኝነት ይተላለፋል። ስለዚህ የጉድፍ ክትባት ያልወሰደ ወይም ጭራሽ ታሞ የማያውቅ ሰው ከታማሚው ጋር የቅርብ ንክኪ ባያደርግ ይመረጣል ።
◈ምርመራዎች ምንድን ናቸው?
▸ ሽፍታውን በማየት እና ስለ ምልክቶቹ በመጠየቅ ስለበሽታው መረዳት ይችላሉ። እንዲሁም ከሽፍታው ላይ ናሙና በመውሰድ ምርመራ ሊደረግ ይችላል።
◈ መከላከያ መንገዶች
• ሕፃናት የጉድፍ መከላከያ ክትባትን እንዲወስዱ ማድረግ
• በአደጉት አገራት ዕድሜያቸው ከ 50 በላይ ለሆኑ ሰዎች የአልማዝ ባለጭራ መከላከያ ክትባትን እንዲወስዱ ይደረጋል።
• የአልማዝ ባለጭራ ታማሚ እስኪያገግምሙ ድረስ ርቀትን መጠበቅ ያስፈልጋል።
• በተለይም የጉድፍ ክትባትን ከአልወሰዱ ወይም በጉድፍ ተይዘው የማያውቁ ከሆነ ይህን ማድረግ ጠቃሚ ይሆናል።
◈የአልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster) ሕክምና
• በቤት ውስጥ የሚደረግ ሕክምና
• ሽፍታው የአለበትን አካባቢ ንጽሕፅህና መጠበቅ፣ በተጨማሪም እርጥበት እንዳይኖር በጥንቃቄ ማድረቅ
• ቆዳን የበለጠ ሊጎዱት ስለሚችሉል እርጥበት ያላቸውን ቅባቶች እና ክሬሞችን ማስወገድ
• የተመጣጠነ ምግብ መመገብ፣ በቂ ዕረፍት ማድረግ
• ሰፋ ያሉ እና ምቾትን የሚሰጡ ልብሶችን መልበስ
• የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ማድረግ፣ ውጥረትን መቀነስ
◈ በሕክምና ተቋማት ውስጥ የሚደረጉ ሕክምናዎች
• የፀረ -ቫይረስ መድኃኒቶች፤ ፣ እነዚህ መድኃኒቶች የቫይረሱን መራባት ለማገድ፣ የሕመሙን ክብደት እና ቆይታ ለመቀነስ እና ሽፍታው በፍጥነት እንዲድን ለማድረግ ያግዛሉ። በተለይም ሽፍታው በተከሠሰተ በ72 ሰዓአታት ውስጥ መወሰድ ከተጀመሩ ውጤታቸው ጥሩ ይሆናል።
• የሕመም ማስታገሻ መድኃኒቶች፤፣ አንዳንድ ጊዜ ሕመሙ ከባድ ሊሆን እና የሕመም ማስታገሻ መድኃኒቶች ሊታዘዙ ይችላሉ።
• የ ፀረ ተሕዋስያን መድኃኒቶች፤ ፣ ቆዳ በበሽታ አምጪ ተሕዋስያን ከተበከለ እና ኢንፌክሽን ከተፈጠረ አንቲባዮቲክስ መድኃኒቶች ይታዘዛሉ።
በዶ/ር ኦሜጋ የተዘጋጀ


