የአባላዘር በሽታዎች ኢንፌክሽን ምንድን ነዉ ?
ምንነቱ ፣ መተላለፊያዎቹን ፣ ምልክቶች ፣ አይነቶቹ ፣ እና መከላከያ መንገዶችን መረዳት በዶ/ር ኦሜጋ
➴ የአባላዘር ኢንፌክሽን (STD) ምንድን ነው?
• የአባላዘር በሽታዎች ማለት በግብረ ሥጋ ግንኙነት ወይም በጠለቀ አካላዊ (ቆዳ) ንክኪ የሚተላለፉ በሽታዎች ናቸው ፡፡
◆ ለአባላዘር በሽታዎች ምን ያህል ተጋላጭ ነን ?
ግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚያደርግ ማንኛውም ሰው ለአባላዘር በሽታዎች ተጋላጭ ቢሆንም በተለይ በማህበረሰባችን ውስጥ በአሁኑ ወቅት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች(ጌይ) ሁለቱንም ጾታ አፍቃሪዎች(ባይሴክሽዋል) እና ከተመሳሳይ ጾታ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚየደርጉ ወንዶቸ በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ ናቸው፡፡ከፍተኛ የቂጥኝ ሕመም ቁጥር ከመኖሩ በተጨማሪ ግማሽ የሚሆነው የኤችአይ ቪ ቫይረስ ኢንፌክሽን የሚከሰተው ከተመሳሳይ ጾታ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት በሚየደርጉ ወንዶች ማኅበረሰብ ውስጥ ነው፡፡
▼ የአባላዘር በሽታዎች እንዴት ይተላለፋሉ?
የአባላዘር በሽታዎች የአባላዘር በሽታ ከያዘው ሰው ወደ ጤነኛ ሰው በወሲብ ወቅት ይተላለፋሉ ይህም በአፍ፣በፊንጢጣ እና በሴት ብልት በሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት እና የመራቢያ አካላት የቆዳ ንክኪን ያጠቃልላል፡፡
እንደ ጨብጥ፣የኤችአይቪ ቫይረስ እና ክላማይዲያ የመሳሰሉት በብልት አካል ፈሳሾች የሚተላለፉ ናቸው፡፡ የኤችአይቪ እና ሔፒታይተስ ቢ ቫይረስ ደግሞ በደም ይተላለፋሉ፡፡
▼ የአባላዘር በሽታዎች እንዴት ይተላለፋሉ?
• የአባላዘር በሽታዎች የአባላዘር በሽታ ከያዘው ሰው ወደ ጤነኛ ሰው በወሲብ ወቅት ይተላለፋሉ ይህም በአፍ፣በፊንጢጣ እና በሴት ብልት በሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት እና የመራቢያ አካላት የቆዳ ንክኪን ያጠቃልላል፡፡
• እንደ ጨብጥ፣የኤችአይቪ ቫይረስ እና ክላማይዲያ የመሳሰሉት በብልት አካል ፈሳሾች የሚተላለፉ ናቸው፡፡ የኤች አይቪ እና ሔፒታይተስ ቢ ቫይረስ ደግሞ በደም ይተላለፋሉ፡፡ ሌሎች የአባላዘር በሽታዎች እንደ ቂጥኝ፣ ጄኒታል ኸርፕስ እና ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ የመሳሰሉት ደግሞ በቆዳ ንክኪ የተላላፋሉ፡፡
▼ የአባላዘር በሽታ አይነቶቹ
ጨብጥ( Syphilis)
ኤች አይ ቪ(HIV)
ቂጥኝ (Gonorrhea)
ከርክር( Chancroid)
ባንቡሌ( Inguinal bubo)
ክላሚድያ( Chlamydia)
ትሪኮሞኒያሲስ( Trichomoniasis)
በብልት አካባቢ የሚወጣ ኪንታሮት (Genital warts)
ፓፒሎማ ቫይረስ(HPV)
ዉሃ የቋጠረ የሚያሳክክ ብዛት ያለው የብልት ላይ ቁስል (Genital herpes)
▼ የአባላዘር በሽታ እንዳለብኝ እንዴት አውቃለሁ?
➴ አብዛኛዎቹ የአባላዘር በሽታዎች ምልክት የማያሳዩ ናቸው፡፡ ስለዚህም ሳናውቀው ሕመሙ ሊይዘን ስለሚችል ማረጋገጥ የምንችለው ምርመራ በማድረግ ብቻ ነው፡፡
እንደ ኸርፕስ ያሉት የአባላዘር በሽታዎች የኤችአይቪ ቫይረስ እንዲተላለፍ አመቺ መንገድ ስለሚፈጥሩ የራስን እና የፍቅር አጋርን ጤንነት ቅድሚያ በመመርመር መጠበቅ ይቻላል፡፡
• ምልክቶችን ካዩ
• ኤች አይ ቪ ምርመራ
• የቂጥኝ (Syphilis) ምርመራ
• የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ምርመራ
• የሄፓታይተስ ሲ ቫይረስ ምርመራ
• የፊንጢጣ፣የጨብጥ እና የክላማይዲያ ምርመራ ማድረግ፡፡
▼ የአባላዘር በሽታ ምልክቶቹ
➴ምልክቶቹ እንደ አባላዘር በሽታዎች አይነቶች የሚለያይ ሲሆን እንደ አጠቃላይ ግን የሚከተሉት ናቸው፡፡
• ብልት ቆዳ ላይ የሚፈጠር ውሃ ያዘለ ወይም የጎደጎደ ቁስል
• ከሴት ብልት የሚወጣ ፈሳሽ
• ህመም እና ማሳከክ
• የሊምፍ ኖዶች ማበጥ
• በሽንት ግዜ የሚሰማ ህመም
• ከፍተኛ ትኩሳት
• የህመም ስሜት
• የከንፈር መቁሰል
• ቆዳ ላይ የሚፈጠር ውሃ ያዘለ ቁስል
▼ የአባላዘር በሽታን መታከም ችላል ?
• አንዳንድ የአባላዘር በሽታዎች እንደ ቂጥኝ፣ ጨብጥ እና ክላማይዲያ ያሉት የአባላዘር በሽታዎች በመድኀኒት የሚድኑ ሲሆን ይህም የሚሆነው የወሲብ ጓደኛችንም ተመርምሮ እና የታዘዘልንን መድኀኒት ጨርሰን ስንወስድ ነው፡፡ ነገር ግን ከዳንን በኋላ ጥንቃቄ የጎደለው ወይም የአባላዘር በሽታ ከያዘው ሰው ጋር የወሲብ ግንኙነት ካደረግን ለአባላዘር በሽታ በድጋሜ ተጋላጭ መሆናችንን መገንዘብ አለብን፡፡
▼ ከአባላዘር በሽታ እራሳችንን እንዴት መጠበቅ ይቻላል ?
ግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚያደርግ ሰው ለአባላዘር በሽታ ተጋላጭ መሆኑን በቅድሚያ መረዳት እና ማወቅ ያስፈልጋል ነገር ግን የአባላዘር በሽታዎችን መተላለፍያ መከላከያ መንገዶችን በመያዝ እንዴት መከላከል እንዳለብን ማወቅ እንችላለን፡፡
• ክትባት በመውሰድ ማንኛውም የወሲብ ግንኙነት የሚያደርግ ሰዉ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ማኅበረሰብ ክፍል ለ ሄፕታይተስ ቢ፣ሄፕታይተስ ሲ እና ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ ከፍተኛ ተጋላጭነት ስላላቸው የሄፕታይተስ ቢ እና የሄፕታይተስ ሲ ክትባት እንዲወስዱ ይመከራል፡፡ በተጨማሪም ማንኛውም እድሜው ከ26 ዓመት በታች ያለ የዚህ ማኅበረሰብ የሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ ክትባት በተጨማሪ እንዲወስድ ይመከራል፡፡
• በየጊዜው ቢያንስ በአመት አንዴ የጤና ምርመራ ማድረግ
• ከማንኛዉም አዲስ የወሲብ ጓደኛ ፍቅረኛ ጋር በግልጽ ስለ አባላዘር በሽታዎች መወያየት እና አብሮ መመርመር ያስፈልጋል።
• ኮንዶምን ማለስለሻዎች ጋር በአግባቡ እና በዘላቂነት መጠቀም
• አደንዛዥ እጾችን ከመጠቀም መቆጠብ


