ሰውነት ማሸማቀቅ | BODY SHAMING
ምንነቱን በመረዳት እና በመቃወም የተሻለ አቃፊ ማህበረሰብ መፍጠር!
አካል-ሰውነት ማሸማቀቅ ምንድነው ?
ስለ አንድ ሰው ወይም ስለ እራስ ሰውነት አሉታዊ አስተሳሰብ ፣አስተያየት ወይም እምነት መያዝ ነው።
እነዚህ አስተያየቶች ስለ ሰውነት ቀለም ውፍረት፣ መጠን ፣ቁመት፣ ዕድሜ ፣ ፀጉር፣ አለባበስ ፣አመጋገብ ፣ ወይም የትኛውንም አካላዊ ሁኔታ ፣ የቁንጅና ደረጃ የሚል መለኪያ በተመለከተ የሚሰጡ ሊሆኑ ይችላሉ!
አካላዊ ማሸማመቀቅ ሁልጊዜም በየቦታው ሊያጋጥም የሚችል ነው በዘመናችን በበዛው የበይነ መረብ ተደራሽነት ደግሞ ነገሩን የበለጠ እንዲገን እና ከብዶ እንዲወጣ አድርጎታል። በእኛ ማህበረሰብ እንደ ኢትዮጵያዊን ወይም እንደ ኩዊር ኮሚኒቲ የእነዚ ተጠቂ ከመሆን አልተከለልንም ይልቅ በዝቶ እና ገዝፎ ቢታይ እንጂ ያነሰ አይደለም። ችግሩ ግን የማህረሰቡ እኔ የኮሚኒቲው ሰውነትን የማሸማቀቅ ምንነት ግንዛቤ ገና ብዙ ሊነገርበት የሚገባ ያልተነካ መሬት ነው።
ስለሌላ ሰው አሉታዊ አስተያየት መስጠት የቡና ቁርሳችን ነው በሀሜት እና በቧልት የተሞላ ባህል ፈጥረን ሁላችን ስለሌሎች አካል ትችት እና ምክር የመስጠት መብት እንዳለን እስክናምን አግባብነትን ረስተናል።
ፊት ለፊት ባንናገር ከጀርባ፣ በፀብ ወቅት ወይም በሌላ ሰው በኩል መልክት ማድረስ እንሻለን።
እያወራን ያለነው ስለማሸማቀቅ ነው ሰዎችን ስለ ማንነታቸው እና ስለአካላቸው ከማድነቅ ባህላችን ይልቅ ማሸማቀቅ እና ማሳፈር ይቀለናል። ለነገሩ ቤት ከመገንባት ማፍረስ ይቀላል!
በሀገራችን ኢትዮጵያ እና በሌሎችም የዓለማት ክፍል ውፍረት እንደ ሀብት የድሎት እና የምቾት ምልክት ተደርጎ ስለሚወሰድ ቅጥነት እንደ ድህነት የማየት ልማድ አለ ከቀጠንክ ምነው ከሳህ አበላም እንዴ ወይም አጥንት ሆንክ ገረጣህ የመሳሰሉ ቃላት ወርወር ይደረጋል። ውፍረት ሆነ ቅጥነት በራሳቸው የምንም ነገር መለኪያ አይደሉም (not medically speaking) ነገር ግን የማህበረሰቡ አመለካከት መዛነፍ ማሳያ እንጂ
አዝባኛው ጊዜ
"የበለጠ ቀጠን ብትዪ እኮ የበለጠ ቆንጆ ትሆኛለሽ "
"ምነው ቀጠንክ ወፈር በል እንጂ "
"ውይ ለወንድ ቀጠንክ ትንሽ ስፓርት ስራ ወንዳወንድ ሁን "
"ይሄን አትልበሺ ቦርጭሽን ያሳያል "
"ምነው ጡትሽ ወረደ ቂጥሽ አነሰ "
"ጥቁር ሆነህ ጥቁር አትልበስ "
"ቆንጆማ ቀይ ሰው ነው"
"እየጦቀርክ ነው አስተጠላብህ"
"ሽንብራ ፀኑር ነው ያስጠላል"
"ሉጫ እና ረዥም ፀጉር ያምራል"
"ለምን ፀጉርሽን ትቆረጫለሽ አጭር ፀጉር ሴት ላይ ያስጠላል"
"ጥብቆ ልብስ አትልበስ ቅጥነትህን ያግለዋል"
"ሰፋ ያለ ልብስ ልበሺ ውፍረትሽን ይደብቃል "
እነዚህን እና የመሳሳሰሉ አስተያየቶች መሰረታዊ ችግራቸው የሚነገረው ሰው የሆነ ልክ ያልሆነ ነገር አንዳለበት የሚያሳዩ መሆናቸው ነው። አዎ ጤንትን ያማከለ ኑሮ መኖር አለብን ግን የሰውን አከል ሰውነት በማሸማቀቅ ለራስ የሚኖርን አመለካከት በአሉታዊ የሚለውጥ መሆኑን አስርፀን ልንገነዘብ ይገባል።
ኩዊርነት እና ሰውነት ማሸማቀቅ
ኪዚህ የወረደ ተግባር ከመሳተፍ የተቆጠብን በሳል ሰዎች ብንሆን ደስ ይለኛል ነገር ግን ብንብስ ነው። በበይነ መረብ መገናኛ መንገድ ላይ የተመሰረትን እንደመሆናችን ፎቶ መላላክ ሮል ኤጅ መጠያየቅ አለ ከዛ ብሶ አሁን ቀለም ቁመት ቅጥነት እያልን እየነስን የመጣንበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው ሰውን እንደ ሰው ከመቀበል ይልቅ በፎቶ አይቶ አይነፋም ይነፋል ያስጠላል እያልን መምረጥ እና መቦለክ እየበዛ ነው።
እኔ በበኩሌ ብዙ ጊዜ ተቦልኬ ተቦልኬ ወቶልኛል አሁን ይህ ተግባር እየጠነከረ ሲሄድ ምን አይነት ኮሚኒቲ ነው የምንሆነው ? ምንድነው እሴታችን የሚሆነው ሰውን ማየት አቅቶን ሰውነት እንደ መለኪያ መጠቀም ጀምረናል ይህ ደግሞ ሴክስ ተኮር የሆነ ኑረት የወለደው ነው። ልናቆም ልንነቃ ይገባል ምን እንደምንናገር እና ስለራሳችን አካል ያለንን አመለካከት መቃኘት አለብን።
እኔ ድሮ በጣም ቀይ መሆን ፈልግ ነበር ሲበዛ ፈረንጅ ሁሉ ባገባ እላለው ቀይነትን የቁንጅና መለኪያ በማድረግ የሚማርከኝ ሰው ሁሉ ቀይ ነው መንገድ ላይ ቀይ ካልሆነ ውስጤ የሚገባ የለም ቢገባም ከስንት አንዴ ነው... በቃ የጎደለኝኝ አካላዊ መለዮ የመመኘት አባዜ ነበር... እያደኩ እና ከራሴ አካል ጋር የጠነከረ ግንኙነት ስመሰርት ቅላት የቁንጅና መለኪያ መሆኑን ተውኩና የራሴን አካል መቀበል ስጀምር ሌሎችን እንዳሉ መቀበልን መማር ጀመርኩ። ለሁሉ ማለት የምፈልገው ከራሳችን አካል ጋር የጠበቀ ግንኙነት እና ፍቅር እንመስርት ያኔ ምናልባት ሌሎችን ከነአካላዊ ሙሉነታቸው ለመቀበል መንገድ ይከፍትልናል።
ለምንድነው ሰውነትን ማሸማቀቅ ትኩረት ልንሰጠው የሚገባው ?
በርካታ በውጪዉ ሀገር የተሰሩ ጥናቶች (በሚያሳዝን መልኩ በሀገራችን የተሰራ የጥናት ስራ በዚ ጉዳይ ላገኝ አልቻልኩም) እንደሚያሳዩን ሰውነት ማሸማቀቅ ለሚከተሉት የአዕምሮ እክል ሊዳርግ እንደሚችል ነው!
ለከፍተኛ ድባቴ የሚዳርግ እንደሆነ
የአመጋገብ ስርዐት ላይ ተፅዕኖ እንደሚያመጣ (eating disorder ) ያስከትላል
በራስ ሰውነት ውስጥ ምቾት ማጣት እና ደካማ በራስ መተማመንን ይፈጥራል
ጭንቀት
የሰውነት ዲስምርፊክ ዲስኦርደር ይዳርጋል (ከተቻላችሁ ይህን በግላችሁ አንብቡት)
የተሳሳተ ስለራሴ ሰውነት አመለካከት በመፍጠር ራስን የማጥፋት ችግር ሊያጋልጥ ይችላል
እና ሌሎች በርካታ ችግሮች ይፈጥራል!
ወሲባዊ ማራኪነትን (sexual attraction )ከሰውነት አንፃር!
እወነት ነው ከሌላ ሰው ጋር የፍቅር ግንኙነት ስንጀምር መጀመሪያ በር ከሚከፍቱ ነገሮች መካከል የሰውነት መለዮዎች ሊሆኑ ይችላሉ አቋሙ መልኩ ምናምን በእኔ አመለካከት አራት ነገሮች የበለጠ ትኩረት ልንሰጠው ይገባል ባይ ነኝ (ከእኔ ብቻ አይደለም | ከጥናቶቼም በመነሳት ነው)
#1 አካላዊ መጣጣም (Physical compatibility ) ምንም አይነት ስሜታዊ ስሜት የማይሰጠኝን ሰው አብሬው ልሆን እንደማልችል ይታወቃል ይህ ማለት ግን የዛን ሰው አካላዊ መለዮዎች በማጣጣል እና type እንዳልሆነ በንቀት በመናገር አይደለም።
እኛም ለሌላ ሰው type እንደማንሆን አምነን በመቀበል የተጎጂነትን ስሜት እንዳይሰማን ማድረግ አለብን ብዬ አስባለሁ አንዳንዴ አካላዊ መጣጣም ስለ ውስጣዊ ኢነርጂም ነው ይሄን መገንዘብ አለብን።
#2 እውቀታዊ መጣጣም (intellectual compatibility ) ይህ ከሌለ ፍቅር ሆነ ግንኙነት አይሰራም! አንድ እውቀት ወይም ዲግሪ ይኑረን ማለት አይደለም ነገር ግን ሌላኛችን የምንናገረውን የምንረዳበት አቅም እና ብስለት በሁለታችንም ውስጥ መኖር መቻል አለበት። ከዛ በላይ ከአጋራችን ወይ ከጓደኛችን የምንቀበለው አዲስ ነገር ከላሌ እና በእሱ የማናድግ ከሆነ in the long run ወደ ተለያዩ አቅጣጫ በማደግ አለመግባባት ሊፈጠር ይችላል ስለዚህ ሰውን እንደ ሰውነቱ መቀበል የሁላችንም ድርሻ ነው ነገር ግን የፍቅር ግንኙነቶችን ስንጀምር በትክክል ትኩረት ሰተን ልንቃኝ የሚገባው aspect ነው።
#ስሜታዊ መጣጣም (emotional compatibility ) ይህን ከሁሉም ነገር አንፃር ልታዩት ትችላላችሁ ከፆታዊ ማንነት ወይም ከወሲባዊ ሚና ወይም ደግሞ የስሜት ብስለት አንፃር ግን ስሜት ማንነት አይደለም (lgbtq+ መሆን ስሜት የያዘ እንጂ በስሜት የሚቋጭ እንዳልሆነ ልብ እያልን) ይሃን ማወቅ አለብን ስሜታችንን ለመግዛት ሁሌ ራሳችንን ማሳደግ አለብን ይህን ስናደርግ ከእኛጋ አብሮ በእዚህ ነገሮች ላይ ተመሳሳይ እሴት ከሌለው ሰው ጋር የፍቅር ግንኙኘቶች መጀመር ችግር እንደሚፈጥር የስነ-ፍቅር-ግንኙነት ባለሙያዎች ያወራሉ።
#የገንዘብ መጣጣም (financial compatibility ) እዚጋ ረገጥ ማለት አለብኝ ብዬ አስባለሁ ኑሮ ውድ ነው ህይወት ከባድ ነው ሶ ሁላችንም በህይወት የራሳችንን ኑሮ የምንኖርበት ራሳችንን የምንችልበት መንገድ መመስረት አለብን ብዬ አስባለሁ።
በዜጋው(LGBTQ+) ኮሚኒቱ የተለመደ እየሆነ የመጣ አንድ ነገር አለ ይህም ሌላ ሰው አስቀምጦ እንዲቀልበን እንዲንከባከበን እና መሬት አትንኩ መባል የሚፈልግ mindset ነው ይህ በታዳጊ ልጆች ብቻ ሳይሆን በሚያስፈራ መልኩ በብዛት እየታየ ያለ ነው
Bitches get a life and work for yourself!!!
አሁን ይህን የማይረባ ደካማ አመለካከት ፊት ካልገፀፅነው መቼ ልንገፅፅው ነው?
ጋብዘኝ ፣ ግዛልኝ ፣ ቤት ተከራይልኝ ፣ ይህን ይሃን አድርግልኝ የሚሉ ጥያቄዎች እና demand ፍቅር ሳይሆን Transaction መሆኑን እንወቅ በሰው መውደድ ድራማ እየሰሩ መበዝበዝ ዋጋ የለሽ የእንጭጭነት መንገድ ነው። ውበት አለ ይረግፋል ለራስ የሚሆን ነገር መጀመር እና skill መፍጠር አለብን
ተማሪ በትምርቱ እየበረታ | ሰራተኛ የተሻለ መንገድ እየጣረ | የግል ሰራተኛ በኔትዎርክ እየሰፋ do what you have to do to have the life you deserve
ሁለቱም አጋሮች የራሳቸው የገንዘብ ምንጭ ሊኖራቸው ይገባል be considerate ራሳችሁን አትጉዱ ሌላ ሰውንም አትበዝብዙ! ራሳችንን መቻል አለብን ስለዚህ ሁላችንም መንቃት አለብን ሰው በጣም የከፋበት ዘመን ነው ፍቅር የሚበል ነገር እያሳየ መውደዱን በጥቅም መካስ የሚፈግበት ዘመን ነው አዝናለሁ ባይሆን ደስ ባለኝ ግን ከሰማውት ካየውት ከገጠመኝ ነው።
ይህን መጥቀሴ ከሰውነት ማሸማቀቅ ጋር ምን ያገናኘዋል? #አላቅም ስፅፈው መጣ ፃፍኩት አለቀ!
ሁሉን አቀፍ የሆነ ኮሚኒቲ እንዴት እንፍጠር?
የራስን ሰውነት ከነ ሙሉነቱ ከነ ምንነቱ መቀበልን መልመድ አለብን ይህን የምናደርገው ስለራሳችን ሰውነት በውስጣችን የሚፈጠሩትን አስተሳሰቦች ከመመልከት እና ከመግራት ይሆናል አስተሳቡን የረጨብን ማንም ይሁን ማን ነቅተን ራሳችንን መቀበል ላይ መስራት አለብን
ሌሎችን ሰዎች በምንመለከትበት ጊዜ ምን እንደምናደንቅ እንመልከት ነገር ግን ሁሌ አካላዊ መለዮች ላይ ብቻ ሳይሆን ከገፅ አልፈን ጠለቅ ብለን መመልከትን እንልመድ እንወቀው እንመልከተው እንደ ሰው
ሮል ኤጅ መጠያየቅ ኖርሜል ነው የኪሎ የቁመት እና የውፍረቱ ነገር ስለ አመለካከታችን የሚናገረው ነገር ስላለ ቆም ብለን ከሎሎች ሰዎች ጋር ያለንን ህብረት ምንመሰርትበትን እሴት እንመልከት።
በጭራሽ ስለሌሎች ሰዎች ሰውነት አሉታዊ ወሬ እናቁም ይልቅ ማድነቅ እና መቀበልን እንጂ
ህብረቶቻቸን በመከፋፈል ፣በመመዳደብ ሳይሆን በመከባበር ፣በመፍቀር ፣በመቻቻል እና በመተሳሰብ ፣በቤተሰባዊ እሴቶች ላይ እንገንባ | ነቃ እያልን አንደ ህይወት ነው ያለን ትርጉም ያለው ህብረት መመስረትን እናስቀድም !
ሀሉን መቀበልን እሴት እናድግር
ሰውን ያለጥቅም መውደድ እሴት እናድርግ
እኔ ብቻ የሚል አመለካከትን ገለን እኛ እንበል!
በዚ ላይ የቀረቡ መረጃዎችን በይበልጥ ጠለቅ አድርጎ ለማንበብ verywellmind.com / withinhealth.com emotional-impacts-of-body-shaming) እንድትመለከቱ አሳስባለሁ።
Book 📖 suggestion to read
#The body is not an apology by Sonya Rene
#Am I Ugly? by Michell Elman
ሰውነት ማሸማቀቅን እቃወማለሁ
ሁሉም ቆንጆ ቅዱስ ውብ ነው!
በሮቢን ኢዮአብ | ማንነት ሚዲያ | ልዩነታችን ለአንድንነት




