ሴታሴት የሆነ ወንድ እንዲሁም ወንዳወንድ የሆነች ሴት ሁላ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ብቻ ናቸው ማለት በፍፁም የተሳሳተ አመለካከት ነው
ይህን ያውቁ ኖሯል?
ይህን ያውቁ ኖሯል?
ሴታሴት የሆነ ወንድ እንዲሁም ወንዳወንድ የሆነች ሴት ሁላ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ብቻ ናቸው ማለት በፍፁም የተሳሳተ አመለካከት ነው።የዚህ አይነት ዝንባሌ ያላቸውን አካላት የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ብቻ አድርጎ መፈረጅ ይበልጥ በኛ ሃገር ላይ ጎልቶ ሲንፀባረቅ ይስተዋላል። ቀደም ብሎ በነበረ ሁኔታ ሴታሴትነት የእድሜ ገደብ ይኖረው ነበረ ያም ማለት "ይሄማ ገና ልጅኮ ነው ምኑን አውቆት ዝም ብሎ ሴታሴት ብቻ ነው"ብለው ለራሳቸው ማስተባበያ የሚያቀርቡ ብዙ የማህበረሰባችን ክፍሎች ነበሩ።
ሴታሴት የምንላቸው ወንዶች ብዙ ሴቶችን በፆታዊ ግንኙነት እንደሚያተራምሱ እያየን እና እየሰማን ያደግን እንኖራለን።እንዲሁም ከተቃራኒ ፆታ ጋር ትዳር መስርተው ልጆችን አፍርተው በሰዎች እይታ ውጤታማ የሚባል ህይወትን ሲመሩ ሴታሴት አባወራዎችን ማየትም የተለመደ ነው።ዛሬ ይበልጥ ሴታሴት ስለሆኑ ቀጥ ወንዶች ለመናገር ፍላጎቱ ያደረብኝ በኛ ማህበረሰብ ውስጥ የዚህ አይነት ዝንባሌ ያላቸውን ልጆችን አሳንሶ የማየት እንዲሁም ከኛ ጋር አንድ ህይወትን የሚጋሩን እስከማይመስል ድረስ ዝቅ አርጎ የመመልከት ትልቅ ችግር እንዳለ ካስተዋልኩ ቡሃላ ነው።አንዳንዶቻችን አርቀን ካለማሰብ ይሁን ነገሮችን ለመረዳት ካለመፈለግ በዚህ ዙርያ ላይ ጭፍን ለመሆን እንሞክራለን ነገ ላይ የሆነ ጥቃት ቢከሰት ወይ በፆታዊ ግንኑነት ወቅት እጅ ከፍንጅ ብትያዙ(የኛን ህይወት ከወንጀል የምትቆጥር ሃገር ላይ ስላለን) አንተ ወንዳወንድ ስለሆንክ እና እሱ ሴታሴት ስለሆነ የሚፈጠር ልዩነት አይኖርም በህግ ፊት እኩል ነው የምትዳኙት ለወንዳወንድነትህ የተለየ የፍርድ ማቅለያ አይኖረውም።ለሴታሴት ወንዶች በፍቅር የሚወድቁ እንስቶች በብዛት እንዳሉ ከኔ በላይ ምስክር ይኖራል ብዬ አላስብም :: በኛም ሀገር ሆነ በውጪው አለም ብዙ በተቃራኒ ፆታ ግንኙነት ውስጥ ያሉ ጥንዶችን መመልከት ያለና የሚኖር ነገር ነው።ለዛሬ በዚህ ርዕስ ዙርያ እንደምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ ጥንዶችን 👇 የፍቅር ታሪክ ይዤላችሁ መጥቻለሁ
እነዚህ ከላይ👆 የምትመለከቷቸው James እና Maren ይባላሉ በ በበይነ መረብ ተገናኝተው በፍቅር የወደቁ እንዲሁም በግንኙነታቸው ኢንተርኔት ላይ ብዙ ሺህ ተከታይን ማፍራት ያሉ ጥንዶች ናቸው።በፍቅር አብረው በዘለቁበቸው ግዜያት በሙሉ ሁለቱም የነበራቸው ደስታ በሌሎች ላይም ተጋብቶ ነበረ።
እንግዲህ ከነዚህ ጥንዶች ብዙ መማር የምንችል ይመስለኛል።አንድ ግዜ ጄምስ "ብዙ ሰዎች አብረን ሲያዩን የትኛዋ ነች ሴት እየሉ ሊየፌዙብን ይሞክራሉ። እኛ መሰረታዊ የሚባለውን የፆታ አተገባበር ስለማናሳይ ተቀባይነት የለንም"ሲል በተደጋጋሚ ይገልፃል። ይህ
አይደለም በኛ ሀገር ባደጉ ሃገራት ላይ እንኳን ምን ያህል ጫና እንዳለ ማሳያ ነው።
ሴታሴት/ወንዳወንድ ለሆኑ ቤተሰቦቻችን አክብሮት እና ፍቅርን በመስጠት ከሰፊው ማህበረሰብ የሚመጣባቸውን ጫና ልንጋፈጥላቸው እንኳን ባንሞክር በኛ እፎይታ እንዲሰማቸው ማድረግ የሁላችንም ሃላፊነት ነው።
ሴታሴት የሆነ ወንድ እንዲሁም ወንዳወንድ ወንድ የሆነች ሴት በሙላ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ አይደሉም!
ባኒ ✍️